ዕድለኛ አይደለሁም
October 25, 2020
ዕድለኛ አይደለሁም

9ኛ ክፍል እያለሁ አንድ ቀን አባቴ ከትምህርት ቤት መልስ እያደረሰኝ ሁሌ እንደምናደርገው ልብ ለልብ እየተጫወትን ነበር። (እየቀለድኩ ነው) ወላጆቼ 6 ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ቤታችንም ሆነ ከቤት ወጪ ሲያደርሱንና ሲመልሱን ጸጥታና ተረጋግቶ መነጋገር የሚያጋጥመን በጣም አልፎ አልፎ ነው። ሁላችንም ብዙ ጉዳዮችን በአንድ ጊዜ ስለምናወራ አሁን እንኳ አንድላይ ስንሰበሰብ ላልለመደው ሰው ከፍተኛ ትንግርት የሆነ ትርምስ ነው። በዚያን ቀን ግን እህቶቼና ወንድሜ በምን አጋጣሚ እንደሆነ ባላውቅም አብረውን ስላልነበሩ ከፓፕስ (አባቴ) ጋር ለማውራት ቻልን። በቀኔ ውስጥ ስላጋጠመኝ አንድ መልካም ነገር ነገርኩትና “ለነገሩ ማክሰኞ የዕድል ቀኔ (my lucky day) ነው” ብዬ ቀጠልኩ። የተወለድኩበትና ከዚህ በፊትም የምቆጥራቸው ብዙ መልካም ነገሮች ማክሰኞ ቀን እንዳጋጠሙኝ በከፍተኛ ደስታ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥቼ ልክ እንደጨረስኩ አባቴ መለስ ብሎ “ይህ ጣዖት አምልኮ ነው” ሲለኝ የተሰማኝን ድንጋጤ እስከዛሬ አስታውሰዋለሁ። አባቴ ቀጥሎም በሕይወታችን ለሚመጡ ማንኛውም መልካም ነገሮች እንደምክንያት የምናቀርበው ክስተቱ የተፈጠረበት ቀን፣ የለበስነው ልብስ (“lucky color”)፣ ከምንወደው ሰው ጋር በመሆናችን ወዘተ… ከሆነ ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር ለሌላ እየሰጠን እንደሆነ ነገረኝ። ሁሌ ከማስታውሳቸው ትምህርቶች አንዱ ነው።

በምን መልኩ ይሆን ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር ለሌሎች ወይም ለራሳችን ስንሰጥ የምንገኘው? በተደጋጋሚ ፈተና የሚሆንብኝ ነገር በተለይ ክርስቲያን ካልሆኑ ወይም የእግዚአብሔርን ሉዓላዊነት ከማይቀበሉ ሰዎች ጋር በሚኖር ውይይት ነው። አንድ መልካም ነገር በሕይወቴ ለምን እንደሆነ ሳስብ ከእግዚአብሔር እጅ የተቀበልኩት ነገር መሆኑን ምንም ጥርጥር የለኝም፤ ግን ይህንኑ ጉዳይ በእግዚአብሔር ላይ ተመሳሳይ እምነት ለሌላቸው ሰዎች ሳካፍል “ይህንን ያደረገልኝ እግዚአብሔር ነው” ብዬ በግልጽ ከመመስከር ይልቅ እንደዕድል፣ ወይም በእኔ ጥረት እንደተገኘ ነገር አድበስብሼው ሳልፍ ራሴን አገኘዋለሁ። ምንም እንኳን የእኛ ማኅበረሰብ ኃይማኖተኛ ቢሆንም ግን ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ ካለው ዓለማዊነት (secularism) የተነሳ ተመሳሳይ እምነት ከማይጋሩ ሰዎች ጋር ስንነጋገር የእግዚአብሔርን ስም ለመጥራት፣ ስላደረገልን ነገር በግልጽ ለመናገር እናመነታለን። በሕይወታችን ያለ ማንኛውም መልካም ነገር የመጣው በሌላ ምክንያት ወይም በራሳችን ጥረትና ጉብዝና እንደሆነ ካሰብን ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር ለሌላ እየሰጠን ነው። አንዳንዴ ደግሞ የውሸት ትኅትናን በመምረጥ መልካም ነገሮቻችንን ሰዎች ሲያነሱ “አይ እሱ እኮ ምንም አይደለም” ብለን እናልፈዋለን – ይህን በማድረግ የእግዚአብሔርን ታላቅ ተዓምርና በጎነቱን እናሳንሳለን።

በዚህ ምድር ላይ ያለን ዋና ተልዕኮ ለሌሎች የእግዚአብሔርን መልካምነት መመስከር፣ ታላቅነትና ጽድቁን ማሳየት ነው። በሕይወታችን የሚታዩት ከእግዚአብሔር የተቀበልናቸው መልካም ነገሮች ለዚህ ተልዕኮ መንገድ የሚከፍቱ ዕድሎች ናቸው። የእግዚአብሔርን ተዓምራትና የእርሱን በጎነት እየቆጠርን እርሱን ስናመሰግን ልባችን በሌላ ምስጋና ይሞላል፣ የሚትረፈረፍ ደስታና አመስጋኝነት መለያችን ይሆናል። ሰዎች ሕይወታችንን በማየትና (በሥራ፣ በቤተሰብ፣ በሀብት፣ በጓደኞች፣ በባህሪያችን፣ በትምህርታችን … ሊሆን ይችላል) እግዚአብሔር ያሳካልንን ነገሮች በመቁጠር “ውይ እንዴት ዕድለኛ ነሽ” ሲሉ፣ ዕድል ሳይሆን ከእርሱ የተቀበልነው ተዓምር መሆኑን በመመስከር የመልካም ስጦታ ትክክለኛው ምንጭ የሆነውን እግዚአብሔርን እንዲያዩ መንገድ እንክፈት።

“ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እርሱ እኔ እንደሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣ እናንተ ምስክሮቼ፣ የመጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ”

በኢሳይያስ 43፡10

Tagged under
<a href="https://beta.selahethiopia.org/author/hannaarayaselassie/" target="_self">Hanna Arayaselassie</a>
Hanna Arayaselassie
Hanna is a "servant of the people" with a big heart for Ethiopia and its ever-growing prospects. She enjoys hosting, charades, and inviting conversations that start with, "Tell me everything about you and your life!"

Latest Articles

Safety from Bullets Seen and Unseen

Safety from Bullets Seen and Unseen

There is no contraption or human being or adoration that can replace the serene and complete love of God. It is that love, that all knowing love, that shields us from “bullets” unseen all day, everyday.

Christian, Repent for Your Sins Against Women

Christian, Repent for Your Sins Against Women

The church has consistently let women and girls down in this country. Dare I say, we have let Christ down in the way we have treated women and the treatment of women we have quietly allowed in and outside of our churches. I believe the body of Christ here in Ethiopia, the local churches that confess the name of Jesus, as well as church leaders, theologians, and prominent Christians need to repent of ongoing sins against women.

He Restores from Calamity

He Restores from Calamity

Yes, we’re home staying away from an invisible virus and we don’t know where it is or how to combat it in our own strength. But as a believer, I’ve been reminded that this is nothing new; I’ve always been fighting with an invisible enemy.